Fana: At a Speed of Life!

ወራሪው ትህነግ በአማራ ክልል 61 ፍርድ ቤቶች ላይ ውድመት አድርሷል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወራሪውና ተስፋፊው የትህነግ የጥፋት ሃይል በአማራ ክልል 61 ፍርድ ቤቶች ላይ ውድመት ማድረሱን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታውቋል።
የፍርድ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታዘባቸው ጣሴ እንደገለጹት አሸባሪው አሸባሪው ቡድን ወረራ በፈጸመባቸው የክልሉ አካባቢዎች ሁሉ በፍትህ ተቋማቱ ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳት በማድረስ ከ140 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት አውድሟል።
አሸባሪው ህወሓት በአማራ እና አፋር ክልል ወረራ በመፈጸም ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል።
ቡድኑ ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች አሰቃቂ ወንጀሎችን የፈጸመ ሲሆን፥ በመሰረተ ልማትና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይም ከፍተኛ ውድመት ፈጽሟል።
በዚህም ሆስፒታሎችና ጤና ተቋማትን ጨምሮ በርካታ ትምህርት ቤቶችን አውድሟል።
በታለ ማሞ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.