Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና የብሉናይል ግዛት በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና የብሉናይል ግዛት ከዚህ ቀደም የነበራቸውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

በአሶሳ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው በኢትዮጵያ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በሱዳን የብሉናይል ግዛት የጋራ የድንበር ልማት ትብብር ውይይት ዛሬ ተጠናቋል፡፡

በውይይቱ ማጠናቀቂያም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና የብሉናይል ግዛት በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ እንዲሁም በሠላም፣ በልማት፣ በህዝብ ግንኙነት ዘርፎች በቀጣይ በጋራ በሚከናወኑ ሥራዎች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን እና የብሉናይል ግዛት ፕሬዚዳንት ጀነራል አህመድ አልዑምዳ ተፈራርመዋል፡፡

በሕዝብ ግንኙነት በሠላም እና የሁለቱን ሕዝቦች ተጠቃሚ በሚያደርጉ በሌሎች መሠል ጉዳዮች ላይ በጋራ ከመስራት ባለፈ፣ አፈጻጸሙ በየጊዜው እየተገናኙ እንደሚገመግሙም በፊርማው ላይ ተገልጿል፡፡

ስምምነቱን በጋራ በመፈጸም የሁለቱን ሃገራት ክልሎች ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከርና ህዝቦቹንም ተጠቃሚ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.