Fana: At a Speed of Life!

የጣሊያን በጎ አድራጎት ድርጅት በምእራብ ጉጂ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ7 ሺህ ኩንታል በላይ በቆሎ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣሊያን መንግሥት በጎ አድራጎት ድርጅት በምእራብ ጉጂ ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 7 ሺህ 500 ኩንታል በቆሎ ድጋፍ ማድረጉን የዞኑ አደጋ ስጋት ሥራ አመራርና የልማት ተነሺዎች ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ኢዮብ ዘሪሁን ለኢዜአ እንዳስታወቁት ቼንትሮ አዩቲ ፕር ኢትዮጵያ የተባለ በጎ አድራጎት ድርጅት ለተጎጂዎቹ ያደረገው ድጋፍ ከ18 ሚሊየን ብር ላይ ግምት አለው።
ድጋፉ በመልካ ሶዳ፣ በሱሮ በርጉዳ፣ በገላና፣ በአባያ፣ በቡሌሆራና በዱግዳ ዳዋ ወረዳዎች በድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እየተከፋፈለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ድርጅቱ በቆሎውን ጉዳቱ ወደ ደረሰባቸው አካባቢዎች ለማጓጓዝ 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ወጪ ማድረጉንም ተናግረዋል፡፡
በዞኑ የበልግ ዝናብ የሚጀምረው በመጋቢት ወር አጋማሽ በመሆኑ የምግብና የእንስሳት መኖ እጥረት ሳይባባስ ድጋፍ እንዲደረግ ኃላፊው ጠይቀዋል፡፡
በዞኑ ድርቅና በጸጥታ ችግር የተፈናቀሉ ከ300 ሺህ በላይ የአርብቶ አደር ቤተሰብ አባላት ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውን አመላክተዋል፡፡
በዞኑ ድርቅ ተባብሶ በቀጠለባቸው ሶስት ወረዳዎች በመኖና በመድኃኒት እጥረት ከ8 ሺህ በላይ የቤት እንስሳት መሞታቸውንና 18 ሺህ 384 የቤት እንስሳት ደግሞ በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.