የሀገር ውስጥ ዜና

ኒጀር የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል በመሆን ባገለገለችበት ወቅት አህጉራችንን አኩርታለች- ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

By ዮሐንስ ደርበው

December 30, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኒጀር የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል በመሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት ባገለገለችበት ወቅት ላሳየችው መርህን፣ ጨዋነትንና የአፍሪካ አንድነትን ማዕከል ያደረገ አቋም አገራችንንና አህጉራችንን ያኮራች በመሆኗ ለኒጀር መንግሥት እና ፕሬዚዳንት ምስጋና እና አድናቆት ይገባታል ሲሉ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቷ ይህን ያሉት የቆይታ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የኒጀርን አምባሳደር ባሰናበቱበት ወቅት ነው፡፡

ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመላክተው÷ አምባሳደሩ ባለፉት ስድስት ዓመታት የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማጠናከር ላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከሰባት ወራት በፊት በኒጀር የሥራ ጉብኝት አድርገው እንደነበርና በ 90 ዎቹ በኒጀር በተካሄዱ ሁለት ምርጫዎች የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የታዛቢዎች ቡድንን መምራታቸው ይታወሳል።