Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ተቋማት ለተፈናቃዮች እና በጦርነቱ ለተጎዱ ዜጎች የ6 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የተለያዩ ተቋማት በአጣየ ከተማ እና አካባቢው ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና ተጎጅዎች 6 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

ቸሻየር ኢትዮጵያ በአጣየ ከተማ አስተዳደር እና በኤፍራታ ግድም ወረዳ ለሚገኙ የአካል ጉዳተኛ ወገኖች 4 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የዓይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የቸሻየር ኢትዮጵያ የፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ኤርሚያስ መኮንን እንደገለፁት፥ ድርጅቱ 200 የአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ኃላፊዎችን እና 600 የቤተሰብ አባላትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ድጋፍ ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡

በሽብር ቡድኑ በተከሰተው ጦርነት ሳቢያ የአካል ጉዳተኞችና ቤተሰቦቻቸው ለከፋ ችግር እንዳይጋለጡ በማሰብ ግምታቸው 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሆኑ ምግብ ነክ እና የንፅህና መጠበቂያ ግብዓቶችን ከመደገፉ በተጨማሪ ለድንገተኛ ውጪ እንዲያገለግላቸው 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ድርጅቱ እነዚህን አካባቢዎች ያቀፈ የመልሶ ማቋቋም ስራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል።

በተመሳሳይ የጋምቤላ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮም በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ሸዋሮት ከተማ በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች 1 ሚሊየን ብር የሚሆን የዓይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ክርምስ ሌሮ የተረፈንን ሳይሆን ያለንን ድጋፍ ይዘን መጥተናል፤ ወገኖቻችን በተለያዩ ሚዲያዎች ካየነውና ከሰማነው በከፋ ሁኔታ ላይ መገኘታቸውን ስለተመለከትን ህብረተሰባችንን በማሳተፍ የመልሶ ማቋቋም ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል አዲስ ዳላስ ኢንዱስትሪስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የአገር ሉዓላዊነትን እያስከበረ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሠራዊት 1ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚጠጋ 4 ሺህ 410 ካርቶን የብስኩት ስንቅ አበርክቷል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.