Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች መቀበያ ፅህፈት ቤት ተቋቋመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች መቀበያ ፅህፈት ቤት ተቋቋመ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 2ኛ ልዩ ስብሰባው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265 /2014 ማጽደቁ ይታወሳል፡፡

በአዋጁ አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 1 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የዕጩ ኮሚሽን አባላትን ከህዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶችና ከሲቪል ማህበራት እንደሚቀበል ተደንግጓል፡፡

በዚህም መሰረት የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ መቀበያ ጽህፈት ቤት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተቋቁሟል፡፡

በአዋጁ አንቀጽ 13 መሰረት ለኮሚሽነርነት የሚያበቁ መሥፈርቶችም፡-

1/ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ፤

2/ ሁሉንም ሃይማኖቶች፣ የተለያዩ ብሔሮችን፣ ብሔረሰቦችን እና ሕዝቦችን በእኩል ዓይን የሚያይ፤

3/ የማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ፤

4/ ለአገራዊ መግባባት ጉልህ አስተዋፅኦ ሊያበረክት የሚችል ፤

5/ መልካም ሥነ-ምግባርና ስብዕና ያለው፤

6/ በሕዝብ ዘንድ ዓመኔታ ያለው፣

7/ በከባድ ወንጀል ተከሶ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያልተላለፈበት፤

8/ የኮሚሽኑን ሥራ በአግባቡ ለመሥራት የሚያስችል የተሟላ ብቃት ያለው፤

9/ ሙሉ ጊዜውን ለኮሚሽኑ ስራ ለማዋል ፍቃደኛ የሆነ የሚሉ ናቸው፡፡

ስለሆነም የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ ፡-

• በቀጥታ ስልክ 0111300340 ወይም 9988
• በፋክስ ቁጥር 0111233007
• በኢ-ሜል dialoguecommission@gmail.com ወይም
• በ info@hopr.gov.et ወይም በአካል በምክር ቤቱ መረጃ እስክሪኑ መስጠት የሚቻል መሆኑን እና በቀጣይ ሶስት ቀናት ውስጥ ጥቆማ የሚሰጥበትን ቅጽ www.hopr.gov.et እንደሚጫን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.