Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴንግ አሎር ጋር ተወያይተዋል።
በወቅቱም አምባሳደሩ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳዮችና ተያያዥ አዳዲስ ሂደቶችን አስመልክተው ገለፃ አድርገውላቸዋል።
ሁለቱም ወገኖች በተለያዩ የሁለቱ አገራት የጋራና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመሥራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም ሀሣብ መለዋወጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ እንደተለመደው በወቅቱ የሚካሄድ ስለመሆኑም አምባሳደሩ ገልጸውላቸዋል ነው የተባለው።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 2 people and people sitting
0
People reached
0
Engagements
Distribution score
Boost post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.