Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ማዕከላዊ ባንክ የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ 13 ነጥብ 43 ቢሊየን ዶላር መደበ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ማዕከላዊ ባንክ ኃላፊ ሱን ጉፌንግ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ÷ የገንዘብ ተቋማት በሀገሪቷ የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ እና ለመቆጣጠር ለሚሰሩ ድርጅቶች የሚያበድሩት 13 ነጥብ 43 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር መድቧል፡፡

ሱን ፌንግ ÷ በቻይና የድንጋይ ከሰል ዋና የኃይል አማራጭ ሆኖ እንደቀጠለ ጠቅሰው ፣ በቀጣይ የድንጋይ ከሰልን የካርበን ልቀት መጠን ለመቀነስ እና ከአካባቢ ብክለት ነጻ የሆኑ ሌሎች የኃይል አማራጮችን ለመጠቀም በትኩረት መስራት ይገባልም ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የቻይና ማዕከላዊ ባንክ የካርበን መጠንን ለመቀነስ ለሚሰሩ ድርጅቶች በዝቅተኛ የወለድ መጠን ብድር ማቅረብ እንደሚቀጥልም ነው ኃላፊው የገለጹት፡፡

የፋይናንስ ተቋማት የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ ለሚሰሩ ተቋማት ካቀረቡት ብድር ውሰጥ የሀገሪቷ ማዕከላዊ ባንክ 60 በመቶውን የገንዘብ አቅርቦት እንደሸፈነ የዘገበው ሲጂቲ ኤን ነው፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.