Fana: At a Speed of Life!

የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 6 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች በአሸባሪው የሕወሃት ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 6 ሚሊየን ብር የሚገመት ምግብ ነክ የሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል።

የጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶች በደቡብ ወሎ በአሸባሪው ህወሓት ቡድን ጉዳት የደረሰባቸውን ተቋማትንም ጎብኝተዋል።

“ጉዳት የደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች በርካታ ናቸው፤ መልሶ የማቋቋም ሥራም የሁላችንም ተግባር ነው” ያሉት ጠቅላይ ጸሐፊው፤ ጉባኤው 300 ኩንታል ዱቄት እና 600 ካርቶን ማኮሮኒ ድጋፍ አድርጓል” ብለዋል።

ለወደፊቱም ሁሉም የእምነት ተቋማት የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ውስጥ የየራሳቸውን አስተዋጽኦ የሚያደርጉ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በድጋፍ ርክክቡ የተገኙት የኢትዮጵያ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ እንዳሉት፥ የሃይማኖት ተቋማት ምዕመናቸውን አስተባብረው ለተጎዱት ወገኖች ድጋፍ ማድረግ ይገባቸዋል።

የሃይማኖት ተቋማት በጉባኤው በኩል ያደረጉት ድጋፍም የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አለመሆኑን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ጻድቁ አብዶ በበኩላቸው፥ በአሸባሪው ቡድን ጉዳት የደረሰባቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች የማቋቋም እና ድጋፍ የማድረግ ሥራ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ግዴታ ነው ብለዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና መስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መሳይ ማሩ፥ በደቡብ ወሎ በጦርነቱ በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለረሃብ መዳረጋቸውን እንዳሳዘናቸው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.