Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በአስተዳደር ወሰን፣ ማንነት እና ራስን በራስ የማስተዳደር ጉዳዮች ላይ ጥናት ማድረጉን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን በአስተዳደር ወሰን፣ ማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጉዳዮች ላይ አገር አቀፍ ጥናት ማከናወኑን አስታውቋል።
 
የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ከ2012 ጀምሮ በአስተዳደር ወሰን፣ የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጉዳዮች ላይ አገር አቀፍ የጥናት እና ምርምር ሲያከናውን መቆየቱን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ይፋ አድርጓል።
 
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናቱን በባለቤትነት ሲመራ መቆየቱንና ሌሎች ችግሮች በሚገኝባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጥናቱ ላይ ተሳታፊ እንደነበሩም ተገልጿል።
 
በጥናቱ በርካታ ምክረሀሳቦች የቀረቡ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በግኝቶቹ መሰረት በቀጣይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ይደረግበታል መባሉን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
 
ከውይይት በኋላ የጥናት እና ምርምር ምክረ ሀሳብ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግም ተገልጿል። ጥናቱ 68 ዞኖች ለማሳተፍ ታስቦ በፀጥታ እና ተባባሪነት ችግር 12 ዞን እና ልዩ ወረዳዎች ላይ ጥናት ማድረግ እንዳልተቻለ ተመላክቷል።
 
ኮሚሽኑ ከትግራይ ክልል ውጭ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳድር ትውውቅ ማድረጉንም ጠቁሟል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.