Fana: At a Speed of Life!

በራያ ቆቦ ሮቢት 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት 19 የተናጠልና የጅምላ መቃብሮች ተገኙ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ራያ ቆቦ ወረዳ በሚገኘው የሮቢት 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት 19 የተናጠልና የጅምላ መቃብሮች ተገኙ።
በወረዳው 129 ትምህርት ቤቶች ዘረፋና ውድመት እንደደረሰባቸው የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
የራያ ቆቦ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መንገሻ በላይነጋ እንደገለጹት፥ በሮቢት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ከተገኙት 19 መቃብሮች ሶስቱ በእያንዳንዳቸው እስከ 30 ሰዎች የተቀበሩባቸው የጅምላ መቃብሮች ናቸው።
ወራሪው ቡድን የወረዳውን ትምህርት ፅህፈት ቤት እና በወረዳው የሚገኙ ሰባት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ 129 ትምህርት ቤቶችን በመውረር ዘረፋ መፈጸሙንና ንብረቶችን ማውደሙን ተናግረዋል።
የሽብር ቡድኑ ከዘረፋቸውና ካወደማቸው ንብረቶችና ቁሳቁሶች መካከልም የቤተ ሙከራ ቁሳቁስ፣ ኮምፒውተሮች፣ ፕላዝማዎች፣ የተማሪ ሰነዶችና ሌሎችም የትምህርት ቤቱ ንብረቶች ይገኙበታል ብለዋል።
የሮቢት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጥበቃ ሰራተኞች አቶ ይመር አየለና ዝናቡ ሰማው ወራሪው ቡድን ትምህርት ቤቱን የመቃብር ስፍራ እንዳደረገው ገልጸዋል።
የሮቢት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለፈው ዓመት መጨረሻ ከ1 ሺህ 800 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምር እንደነበር ተገልጿል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.