Fana: At a Speed of Life!

የአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ነገ ይመረቃል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የተገነባው የአብርሆት ቤተ-መፃህፍት ነገ ይመረቃል፡፡
በአዲስ አበባ 4 ኪሎ በዘመናዊ መልኩ የተገነባው ቤተ መፃህፍት የማንበብ ባህልን ለማዳበር ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተመላክቷል።
ቤተ መፃህፍቱ በነገው እለት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የሚመረቅ ይሆናል።
በአንድ ጊዜ ከ2 ሺህ በላይ ተጠቃሚዎችን ማስተናገድ የሚችለው ቤተ መፃህፍት በውስጡ ከማንበቢያ ስፍራ በተጨማሪ፥ 8 የመጽሐፍ መሸጫ ሱቆች፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ ካፍቴሪያ፣ የህፃናት ማንበቢያ ስፍራዎችን ያካተተ ነው።
ከዚህ ባለፈም የተለየ ፍቃድ ያላቸው ሰዎች የሚያነቡበት የመጽሐፍ ክፍል እንዳለው የቤተ መፃህፍቱ ፕሮጀክት ማናጀር ታሪኩ ታደሰ ተናግረዋል፡፡
ቤተ መፃህፍቱ የተሟላ የመኪና ማቆሚያ እንዳለውም ተገልጿል፡፡
የቤተ መፃህፍቱ ግንባታ በ18 ወራት መጠናቀቁም ነው የተገለጸው።
በታሪኩ ለገሰ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People reached
27
Engagements
Boost post
26
1 Comment
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.