Fana: At a Speed of Life!

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ከሶስት ወራት በኋላ ወደ መደበኛ መማር ማስተማር ስራ ይመለሳል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወሎ ዩኒቨርሲቲ ከሶስት ወራት በኋላ ወደ መደበኛ መማር ማስተማር ስራ እንደሚመለስ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር አስታወቀ፡፡
አሸባሪው ህወሃት በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ጭምር በወሎ ዩኒቨርሲቲ 11 ቢሊየን ብር ግምት ያላቸው ንብረቶችን ማውደሙን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር መንገሻ አየነ ተናግረዋል፡፡
የህክምና፣ የተፈጥሮ ሳይንስና የምህንድስና ቤተ ሙከራዎችን ጨምሮ ከውጭ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር የተገነቡ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ማዕከላት በአሸባሪ ቡድኑ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል፡፡
 
በተጨማሪም የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና የአይሲቲ መሰረተ ልማቶችን መዝረፉንና መውሰድ ያልቻላቸውን ደግሞ አገልግሎት እንዳይሰጡ አድርጎ ማውደሙን አብራርተዋል፡፡
 
የደረሰውን ውድመት መልሶ በመገንባት ዩኒቨርሲቲውን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችሉ ስራዎች መጀመራቸውን ጠቅሰው፥ በዚህም የመማር ማስተማር ሂደቱ ከሶስት ወራት በኋላ በድጋሚ እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡
 
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ከመጀመሪያ ዲግሪ አንስቶ እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ድረስ ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ እንደነበር ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.