Fana: At a Speed of Life!

በህዳር ወር ከወጪ ንግድ 333 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 በጀት ዓመት በህዳር ወር ከወጪ ንግድ 333 ሚሊየን 932 ሺህ ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለፀ፡፡
በወሩ ከግብርና፣ ከማምረቻው ዘርፍ እና ከማዕድንና ሌሎች ምርቶች ነው 333 ሚሊየን 932 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በማግኘት የዕቅዱን 99 ነጥብ 95 በመቶ ማሳካት የተቻለው፡፡
ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር በ42 ነጥብ 48 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በበጀት ዓመቱ ህዳር ወር ከተያዘው ዕቅድ በላይ አፈጻጸም ያስመዘገቡት የወጪ ምርቶች ቡና፣ የቅባት እህሎች፣ ቅመማ ቅመም፣ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ ምግብ መጠጥና ፋርማሲዮቲካልስ፣ ኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓት፣ ስጋና የወተት ተዋጥጻኦ እና ኤሌክትሪክ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.