Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ ምክክሩ በህዝቦች መካከል ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር እንጂ ከአሸባሪዎች ጋር መደራደርን ታሳቢ ያደረገ አይደለም – አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ ምክክሩ በህዝቦች መካከል ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር እንጅ ከአሸባሪው ህወሃት ጋር መደራደርን ታሳቢ ያደረገ አይደለም ሲሉ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናገሩ፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው በፈረንጆች 2021 ከኢትዮጵያ አለማቀፍ ግንኙነት ጋር በተያያዘ የተሰሩ ስራዎችን እና በቀጣይ 2022 የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያና በሌሎች በርካታ ጉዳዮች ላይ ከ”ሆርን ሪቪው” ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል።
አምባሳደር ሬድዋን በዚህም ወቅት የውስጥ ችግሮችን መፍታት የውጭ ጫናዎችን ለመቋቋም እንደሚያስችል አስገንዝበዋል፡፡
በቃለ መጠይቁ ላይ በመጀመሪያ ብሔራዊ መግባባት በሚለው ሀሳብ ላይ ግልጽነት ሊኖር ይገባል ብለዋል ሚኒስትር ድኤታው።
ይደረጋሉ ተብለው የታሰቡት አገራዊ የምክክር መድረኮች በህዝቡ እና በፖለቲካ ልሂቃኑ መካከል የጋራ መግባባት ማስፈንን ታሳቢ ያደረገ ነው፤ ይህ ማለት ግን አሸባሪ ከተባሉ አካላት ጋር መደራደር ማለት አይደለም ብለዋል።
የህውሃት ስሪት ለአመጽ እንጅ ለሰላም የሚመች አይደለም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፥ የየትኛውም ሀገር መንግስት ከአሸባሪ ድርጅት ጋር ሲደራደር አይተን አናውቅም እኛም፤ አንደራደርም ነው ያሉት፡፡
የመደበኛነት እና መልሶ ማቋቋም ስራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል ግልጽ ሁኔታዎችን እና ደረጃዎችን ማውጣት የኢትዮጵያ መንግስት ሃላፊነት መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.