Fana: At a Speed of Life!

የሐረማያ እና ዲላ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ መስኮች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች አስመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ እና ዲላ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ መስኮች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች አስመረቁ፡፡
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በጤናና ህክምና ሳይንስ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 411 ተማሪዎች አስመርቋ፡፡
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለ66ኛ ጊዜ ለጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጁ ደግሞ ለ24ኛ ጊዜ ተማሪዎችን ማስመረቁን ከዩኒቨርስቲው የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተመሳሳይ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ25ኛ ዙር በተለያዩ ሙያ ያሰለጠናቸውን 270 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ከህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተጨማሪ በተለያ ምክንያት በተከታታይና መደበኛ መርሃ ግብር የተማሩ እና ሳይመረቁ የቆዩ 272 ተማሪዎችን ጨምሮ በድምሩ 542 ተማሪዎችን ነው ዛሬ ያስመረቀው፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ችሮታው አየለ÷ ተመራቂዎች ሀገራቸውን እና ወገናቸውን በሙያዊ ስነ ምግባር እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።
በምረቃው የተገኙት የዲላ ከተማ ከንቲባ አቶ ተስፋጽዮን ዳካ በበኩላቸው÷ ተመራቂዎች ሀገር በምትፈልጋቸው ወሳኝ ወቅት መመረቃቸውን ጠቁመው÷ በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የገበዩትን እውቀትና ክህሎት በላቀ ደረጃ መጠቀም እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
ኮሌጁ በፋርማስ የትምህርት ዘርፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን አስመርቋል።
በማስተዋል አሰፋ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.