Fana: At a Speed of Life!

የዓለም የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ውድድርን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ ሪከርድ በመስበር አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድርን በሪሁ አረጋዊና እጅጋየሁ ታዬ ሪከርድ በመስበር ጭምር አሸነፉ፡፡
በፈረንጆቹ የ2021 የመጨረሻዋ ቀን በስፔን ባርሴሎና በተደረገ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በሁለቱም ፆታ ኢትዮጵያውያኑ ሪከርድ ሰብረው ማሸነፋቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በሪሁ ውድድሩን በ12:49 በሆነ ሰዓት እንዲሁም፥ እጅጋየሁ በ14:19 በሆነ ሰዓት የርቀቱን የዓለም ሪከርድን ጭምር በማሻሻል ነው ያሸነፉት፡፡
በተመሳሳይ በብራዚል ሳዎፖሎ በተደረገ ኮርዲያ ዲ ሳዎ ሲልቨስተር 15 ኪሎ ሜትር ውድድር በወንዶች፥
በላይ በዛብህ አንደኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ፥ በሴቶች ደግሞ የኔነሽ ድንቄሳ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።
በስፔን ማድሪድ በተደረገ የሳን ሲልቨስተር ቫሊካና 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ደግሞ በሴቶች፥ ደጊቱ አዝመራው አንደኛ በሆኑ አጠናቃለች።
በሌላ መርሃ ግብር በጣልያን ቦላኖ በተደረገ ቦ ክላሲክ በወንዶች 10 ኪሎ ሜትር ውድድር፥ ታደሰ ወርቁ አንደኛ እና ታምራት ቶላ ሁለተኛ ሆነው ውድድሩን ጨርሰዋል፡፡
በሴቶች 5 ኪሎ ሜትር ውድድር ደግሞ ዳዊት ስዩም አንደኛ በመሆን አጠናቃለች፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.