Fana: At a Speed of Life!

የአብርሆት ቤተ መፃህፍት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአብርሆት ቤተ መፃህፍት ተመረቀ፡፡
በአዲስ አበባ 4 ኪሎ ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ በዘመናዊ መልኩ የተገነባው ቤተ መፃህፍት የማንበብ ባህልን ለማዳበር ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተመላክቷል።
ቤተ መፃህፍቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና አዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ መርቀው ከፍተውታል፡፡
በአፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ አስር ቤተ መፃህፍት አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት አብርሆት ቤተ መጽሐፍት በአራት ወለሎች ተከፍሎ በውስጡ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን መጽሐፍት የሚይዝ መደርደርያ ተገጥሞለታል፡፡
ከ240 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወረቀት አልባ መጽሐፍትና 300 ሺህ ጥናታዊ ፅሑፎች የያዘ ነው፡፡
የህፃናት ማንበብያ ስፍራን ጨምሮ የአይነ ስውራን ማንበቢያ ቦታና የብሬል መጽሐፍት ይገኙበታል፡፡
አምፊ ትያትር እና መጫዎቻ ስፍራዎች እንዲሁም ከ120 በላይ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ መመገቢያ ካፌ፣ ስምንት የመጻህፍትና ተጓዳኝ አገልግሎት መስጫ ሱቆች ይገኙበታል፡፡
በታሪኩ ለገሰ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.