Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ም/ቤት ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችና ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችን እና ደንቦችን እንዲሁም ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ።
 
ለሁለት ቀናት በተለያዩ ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ሲመክር የቆየው የክልሉ ምክር ቤት መደባኛ ጉባኤ፥ የክልሉን ቀጣይ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድን ጨምሮ የተለያዩ አዋጆች እና ደንቦች ላይ ሰፊ ውይይቶችን በማድረግ አፅድቋል።
 
በመጨረሻም በተጓደሉ የቢሮ ኃላፊዎች ምትክ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የቀረበ ሹመትን አፅድቋል።
 
በዚህም መሰረት፥ ወ/ሮ እመቤት ኢሳያስ የክልሉ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ እና አቶ ተሻለ ዮና የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።
 
በተጨማሪም የምክር ቤቱን ቋሚ ኮሚቴዎች ሰብሳቢዎችንና ምክትል ሰብሳቢዎችን በመምረጥ እና በማፅደቅ መደበኛ ጉባኤው ተጠናቋል።
 
 
በቢቂላ ቱፋና ታመነ አረጋ
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.