Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ ዓመት ስለ ኒውክሌር ጦር መሣሪያና አሜሪካ የምናወራበት ሳይሆን ስለ ትራክተር ፋብሪካዎቻችን የምናስብበት ነው – ኪም ጆንግ ኡን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን አዲሱ ዓመት ስለ አሜሪካ እና ስለ ኒውክሌር ጦር መሣሪያዎቻችን የምናወራበት ሳይሆን ስለ ትራክተር ፋብሪካዎች እና ስለ ተማሪዎች ዩኒፎርም የምናስብበት ይሆናል አሉ።

ኪም ጆንግ ኡን ይህን የተናገሩት ሥልጣን ከያዙ 10ኛ ዓመት መድፈናቸውን አስመልክቶ በተዘጋጀ ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ነው፡፡

መሪው የሀገራቸው የ2022 ዋና ግብ ልማት ላይ አተኩሮ በመሥራት የዜጎችን ሕይወት ማሻሻል እንደሆነም አስምረውበታል፡፡

ኪም በአዲሱ ዓመት ከደቡብ ኮሪያ እና ከአሜሪካ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመጀመር ማቀዳቸውም ተመልክቷል።

የኪም አብዛኞቹ የ10ኛ ዓመት ክብረ በዓል ንግግሮች በሀገር ውስጥ ጉዳዮች፣ በገጠር ልማት ዕቅድ ትግበራ፣ በምግብ ራስን ስለመቻል፣ በትምህርት ቤት ዩኒፎርም እና በማኅበረሰባዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮሩ ነበሩ ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.