Fana: At a Speed of Life!

ወደ ሀገር ቤት-የዳያስፖራ ፌስቲቫል ዛሬ በተመረቀው አፍሪካ ፓርክ በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ሀገር ቤት – የዳያስፖራ ፌስቲቫል ዛሬ በተመረቀው አፍሪካ ፓርክ በይፋ ተጀምሯል።
 
በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ ሌሎች ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት የሥራ ሃላፊዎች እና ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል።
 
በስነ ስርዓቱ ላይ የአፍሪካ ፖርክን ጨምሮ የኢትዮጵያ እና የአዲስ አበባ ፓርኮችም ከዛሬ ጀምሮ ለህዝብ ክፍት በመሆን አገልግሎት እንደሚሰጡ ተነግሯል፡፡
 
በፓርኩ የተለያዩ ታሪካዊ፣ ባህላዊና አገራዊ ዝግጅቶች ለጎብኚዎች የቀረቡ ሲሆን፥ የመዝናኛ ፕሮግራሞችም ተዘጋጅተዋል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.