Fana: At a Speed of Life!

በእስራኤል የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ለመልሶ ግንባታና ማቋቋም ሥራ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በእስራኤል የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት በመልሶ ግንባታና ማቋቋም ሂደት ተሳትፎ ማድረግ የሚያስችል ስራ መጀመራቸውን የቀድሞ የእስራኤል ፓርላማ (ክኔሴት) አባል ሽሎሞ ሞላ ገለጹ።
የቀድሞው የክኔሴት አባሉ ሽሎሞ ሞላ በእስራኤል የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላት ፣መንግስት አሸባሪው ህወሃት በአማራና አፋር ክልሎች ወረራ በፈጸመበት ወቅት ያደረሰውን ውድመት መልሶ ለማቋቋም ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ለኢዜአ ገልጸዋል።
በእስራኤል የሚገኙ ዳያስፖራዎች በተለይም የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ውድመት በደረሰባቸው አካባቢዎች መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ ኢኮኖሚውን እንዲያነቃቁ ቅስቀሳ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው ፥በዚህም የታየውም ፍላጎት አበረታች የሚባል እንደሆነ ተናግረዋል።
አያይዘውም ሐኪሞች፣ መሐንዲሶችና በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ ባለሙያዎች በሙያቸው ኢትዮጵያን ማገዝ ይፈልጋሉ፤ መንግስትም ባለሙያዎቹ አገራቸውን የሚያገለግሉበት አሰራር እንዲዘረጋ ጠይቀዋል።
“ኢትዮጵያ በዘላቂነት የኢኮኖሚ እድገቷን ማረጋገጥ የምትችልበት የውሃ፣ መሬትና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶች አሏት” ያሉት ሽሎሞ ፥ ይህን አቅም ለመጠቀም የሚያስችል ቴክኖሎጂዎች አስፈላጊ መሆናቸውን አመልክተዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.