Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ወለጋ ዞን ከ300 በላይ የሸኔ አባላት ለመንግስት እጃቸውን ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን 312 የአሸባሪው ሸኔ አባላት ለመንግስት እጃቸውን ሰጥተዋል።
አባላቱ የሽብር ቡድኑ በህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን እኩይ ተግባር በመገንዘብ ነው በአባ ገዳዎች የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው በሠላም ለመንግስት እጃቸውን የሠጡት።

የምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ተስፋዬ እንደገለጹት፥ እጃቸውን ከሰጡት የሽብር ቡድኑ አባላት ጋር የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እና ገንዘቦች ተይዘዋል።

እጃቸውን የሰጡት የሸኔ አባላት በዞኑ ሳሲጋ እና ዲጋ ወረዳዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.