Fana: At a Speed of Life!

‘ስለ ኢትዮጵያ’ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ ከነገ ጀምሮ ለእይታ ይበቃል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ‘ስለ ኢትዮጵያ’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀው የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ ከነገ ጀምሮ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ለእይታ ይበቃል።
አውደ ርዕዩ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ አገርን ለማዳን ያደረጉትን ተጋድሎ ያሳያል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ታደሰ፥ አውደ ርዕዩ ድርጅቱ ላለፈው አንድ ዓመት ለሁለት ወር በዘለቀው ጦርነት በፎቶ የሰነዳቸውን ኩነቶች የሚታዩበት እንደሆነ ለኢዜአ ገልጸዋል።
በትግራይ ክልል የአገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ከሕዝቡ ጋር የነበረው መስተጋብርና ያበረከተው አስተዋጽኦ፣ የደረሰበት ጥቃትና ጉዳት እንዲሁም አገርን ለማዳን የከፈለውን መስዋዕትነት የሚሳዩ ፎቶዎች በአውደ ርዕዩ ላይ እንደሚታዩ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ያደረገው ድጋፍ እንዲሁም አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች ፈጽሞት በነበረው ወረራ በዜጎች ላይ ያደረሰውን አሰቃቂ ድርጊቶችና በተለያዩ ተቋማት ላይ ያደረሰውን ከፍተኛ ውድመትና ዝርፊያ የሚያሳዩ ፎቶዎች ለሕዝብ እይታ ይቀርባሉ ብለዋል።
አውደ ርዕዩ ‘ኢትዮጵያ አሸንፋ ትሻገራለች’ የሚለውን እሳቤ የያዘ እንደሆነና በዚህ ረገድም “ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ኢትዮጵያን ለማዳንና የጠላትን አገር የማፍረስ እኩይ አላማ ለማክሸፍ ያደረጉትን ተጋድሎ” የሚሳይ መሆኑን ነው አቶ ጌትነት የገለጹት።
ከታህሳስ 25 እስከ ጥር 12 ቀን 2014 ዓ.ም የሚቆየውን አውድ ርዕይ ኢትዮጵያውያን፣ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት፣ የውጪ አገር ዜጎች፣ ዲፕሎማቶችና ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
124
Engagements
Boost post
113
3 Comments
8 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.