Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሲያካሄዱት የነበረው ውይይት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሶስት ቀናት ሲያካሄዱት የነበረው ውይይት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቅቋል።
በውይይቱ ከድህረ-ጦርነት በኋላ የሚከሰተውን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በብቃት ለመምራት የሚያስችል የአመራር ዝግጅት እንዲኖር አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚኖሩ ተላላኪ ቡድኖች ላይ የተጀመረው የተቀናጀ እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧልም ነው የተባለው።
ክልሉ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መገኛ እንደመሆኑ ለክልሉ ሰላም አመራሩ ከፀጥታ ኃይሉና ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት መስራት እንዳለበት ተመላክቷል።
በአሸባሪው የህወሓት ቡድን የወደሙ ተቋማትንና ከቀያቸው የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋም እንደሚሰራም ተጠቅሷል።
የሰብዓዊና ቁሳዊ ድጋፍ ለማድረግ ክልሉ ከፌደራል ጋር የጀመረውን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ መቀመጡን ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.