Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራዎች ጦርነቱ የተካሄደባቸውን አካባቢዎች ለመጎብኘት ሰመራ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ጥሪ የተቀበሉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጦርነቱ የተካሄደባቸውን አካባቢዎች ለመጎብኘት ሰመራ ገብተዋል።
በኢትዮጵያ ዳያስፓራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሀመድ ኢድሪስ የሚመራው ቡድን ከዳያስፓራዎቹ ጋር በመሆን ነው አካባቢዎቹን ለመጎብኘት ሰመራ የገቡት።
በቀጣይ ቀናት በአማራና አፋር ክልሎች በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችንና ነዋሪዎችን ይጎበኛሉ ተብሎም ይጠበቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አንድ ሚሊየን ዳያስፓራዎች የውጭውን ጫና ለመቀልበስ ወደ ሀገር እንዲገቡ ባደረጉት ጥሪ መሠረት በርካቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል።
በሀብታሙ ተ/ስላሴ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.