Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን ለቀቁ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣  2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  የሰዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ስልጣን መልቀቃቸውን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሱዳን ህዝብ ባስተላለፉት መልዕክት ስልጣን መልቀቃቸውን ይፋ አድርገዋል።

ሱዳን በቅርቡ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ማድረጓን ተከትሎ በፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች።

መፈንቅለ መንግስት ያደረገው ወታደራዊ ሀይሉ አስሯቸው የነበረውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክ ከእስር ፈቶ ወደ ስልጣን ቢመልሳቸውም የዚያች ሀገር የፖለቲካ ቀውስም ሆነ ህዝባዊ ተቃውሞ ጋብ ማለት አልቻለም።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከወታደራዊ መሪው አል ቡርሃን ጋር የደረሱት ስምምነት በሲቪሉ የፖለቲካ ስብስብ ዘንድ አልተወደደም።

በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሱዳን ፖለቲካ ላይ ተፅእኖ ማድረግ እንደተሳናቸው እና የገቡትን ቃል መጠበቅ ባለመቻላቸው ስልጣን ለመልቀቅ መገደዳቸውን ተናግረዋል።

የዚያች ሀገርም የፖለቲካ ቀውስም እንደቀጠለ ነው።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.