የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ አፍሪካ ስዌቶ የወጣቶች እንቅስቃሴ መሪ ሎንታታ ላክስ አዲስ አበባ ገባ

By Meseret Awoke

January 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ ስዌቶ የወጣቶች እንቅስቃሴ መሪ ሎንታታ ላክስ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገባ።

የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቀኙ ወጣቱ ላክስ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው #የበቃ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ብቻ ተገድቦ እንዳይቀርና ዘላቂነት እንዲኖረው ለማድረግና ያለውን ልምድ ለማካፈል ነው።

ላክስ በተለይ አፍሪካዊያን ወጣቶች የውጭ ጫናዎችን እንዴት መቋቋም እንዳለባቸውና ባዕድ ሀሳብ እንዳይገዛቸው የሚታገል ወጣት ነው።

ወጣቱ በደቡብ አፍሪካ ወጣቶችና የተለያዩ ተቋማት ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ሲሆን ‘የአፍሪካውያን ችግር በአፍሪካውያን መፈታት አለበት’ የሚል ጽኑ አቋም አለው።

ላክስ ወደሚወዳት የአፍሪካ እናት ኢትዮጵያ በመምጣቱ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።

ላክስ በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የጠቅላይሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተወካይ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ እና የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ፅጌሬዳ ዘውዱ ተቀብለውታል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!