የሀገር ውስጥ ዜና

ማለዳውን ከዲሲ ወደ አዲስ አበባ እየበረረ ባለ አውሮፕላን ውስጥ ያሉ ተሳፋሪዎች የ10 ሺህ 400 ዶላር ድጋፍ አደረጉ

By Meseret Awoke

January 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ማለዳውን ከዲሲ ወደ አዲስ አበባ እየበረረ ባለ አውሮፕላን ውስጥ ያሉ ተሳፋሪዎችን በማስተባበር የ10ሺህ 400 ዶላር ድጋፍ በማሰባሰብ በአይዞን ኢትዮጵያ አካውንት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉን ያስተባበሩት በበረራው የነበሩ የተወሰኑ ተጓዦች ሲሆኑ፥ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕልንማረፊያ በሚገኘው የአይዞን ኢትዮጵያ የንግድ ባንክ ሂሳብ ገቢ እድርገዋል።

በርካታ ኢትዮጵያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተደረገላቸው ወደ ሃገር ቤት ግቡ ጥሪ ምላሽ እየሰጡ ናቸው።

ወደ ሃገር ቤት የሚገቡትም በተዘጋጀው የድጋፍ ማሰባሰቢያ ማእከላት በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች መልሶ ማቋቋም እና ለወደሙ ተቋማት ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።

በቆንጅት ዘውዴ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!