Fana: At a Speed of Life!

ጁንታው በአፋር ክልል ያደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ ለዳያስፓራው ገለፃ እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር ውስጥ ለገቡ ኢትዮጵያውን ዳያስፖራዎች አሸባሪው የህወሓት ቡድን በጋሊኮማ ኡዋ በራህሌ እና ሌሎች አካባቢዎች ያደረሰው ጭፍጨፋ እና ውድመትን የተመለከተ አውደ ርዕይ ቀረበ፡፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በጋሊኮማ ኡዋ በራህሌ እና ሌሎች አካባቢዎች በከባድ መሣሪያ ያደረሰው ጅምላ ጭፍጨፋ፣ በእናቶች ህፃናት እና አዛውንቶች ላይ የደረሰው ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ፣ ቁርአንን ማቃጠል ጨምሮ በመስጊዶች ላይ ያደረሰው ከባድ ጉዳት፣ በጤናው ዘርፍ የደረሰው ከፍተኛ ኪሳራ፣ በውሃና መስኖ መሠረተ-ልማት ዘርፍ ፣ በትምህርት ዘርፍ እንዲሁም በእርሻ ተፈጥሮ ሐብት ላይ አሸባሪ ቡድኑ ያደረሰው ከባድ ኪሳራ ጥፋትና ውድመት የሚያስቃኝ ዓውደ ርዕይ ለዳያስፖራ ኢትዮጵያውን እንደቀረበና ማብራሪያም እንደተሰጣቸው ነው የተገለጸው፡፡

ቡድኑ በየዘርፎቹ ያሳየው ርካሽነትና ሰይጣናዊነት የአፋር ህዝብ ላይ ያደረሰው ጉዳት ተብራርቶላቸዋል።

ከሰውነት በራቀ ያደረሰው ውድመትም በእጅጉ የቡድኑን ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ ማሳያ ስለመሆኑም በገለጻው ተነስቷል።

ኤግዚቢሽኑ “ዳያስፓራና ሀገር ግንባታ” በሚል ርዕስ ከሚካሄደው የምክክር መድረክ ጎን ለጎን የቀረበ መሆኑም ተመላክቷል።

በምክክር መድረኩ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባ፣ የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዱአለም፣ ሚኒስትር ዴኤታው ታዬ ደንደኣ እንዲሁም ሌሎችም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የሀገርን ጥሪ ተቀብለው የመጡ ዳያስፓራዎች በጦርነቱ የተጎዱ የአፋርና አማራ ክልሎችን ለመጎብኘት ትላንት ሰመራ መግባታቸው ይታወሳል።

በሐብታሙ ተ/ስላሴ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.