Fana: At a Speed of Life!

“ዳያስፖራና ሀገር ግንባታ” በሚል ርእስ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ዳያስፖራና ሀገር ግንባታ” በሚል ርእስ የምክክር መድረክ በሰመራ እየተካሄደ ነው፡፡
በምክክሩ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባ፣ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱአለም፣ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታው ታዬ ደንደኣ እንዲሁም ሌሎች የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በመድረኩ አቶ አወል አርባ ÷በአሸባሪው ህወሃት ቡድን ላይ ለተገኘው ድል ዳያስፖራው የራሱ ሚና እንደነበረው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን በአፋር በኩል መድፈር ፈፅሞ የማይሞከር መሆኑን ጠላቶቻችን ሊያውቁ ይገባል ያሉት ርእስ መስተዳድሩ  አሸባሪ ቡድኑ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ቀንደኛ ጠላት መሆኑን በተግባር አሳይቷልም  ነው ያሉት፡፡

የዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሃመድ ኢድሪስ  በበኩላቸው ሀገር በመገንባት ሂደት የዳያስፖራው ተሳትፎ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።

 

የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም በበኩላቸው፥ የሽብር ቡድኑ የባእድ ወራሪዎች እንኳን የማይፈፅሙትን ለመስማት ሚዘገንኑ በደሎችን መፈፀሙን ነው ያነሱት።

ከባድ መሳሪያን ህፃናት ላይ በማዝነብም በምንም የማይተካ የሰው ህይወትን ቀጥፏል፤ ኢትዮጵያንም ለማዋረድ የቻለውን ሞክሯል ብለዋል።

“ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያኑ ከየትኛውም ጊዜ በላይ ፈተና ውስጥ ባለችበት ወቅት በመምጣታቸሁ ትርጉም ያለው ነው ታሪኩንም በጀብዱ ትጋሩታላችሁ” ነው ያሉት።

የዳያስፖራ ማህበረሰቡ ለሀገሩ ድምፅ በመሆን የፈፀመው ተጋድሎም ታሪክ እንደማይረሳው አቶ ብናልፍ አንስተዋል።

የሀገርን ጥሪ ተቀብለው የመጡ ዳያስፓራዎች በጦርነቱ የተጎዱ የአፋርና አማራ ክልሎችን ለመጎብኘት ትላንት ሰመራ መግባታቸው ይታወሳል።
በሀብታሙ ተክለስላሴ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.