Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰጠውን ድጋፍ ለመወሰን የወጣው መመሪያ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተወያየ ነው።
የመመሪያው መሻሻል መንግስት ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰጠውን ድጋፍ በቀጣይነት በአዋጁ መሰረት የሚመደብበትን ሁኔታ፣ የሚከፋፈልበትን መስፈርት፣ ቀመር እና አጠቃቀም እንዲሁም አስተዳደር በተመለከተ ግልጽ አሰራርን ለመዘርጋት ነው ተብሏል።
ከዚህ ባለፈ የፖለቲካ ፓርቲዎች የዜጎችን ሃሳብ በተደራጀ መንገድ መግለጽ እንዲችሉ እና በአሰራራቸውም የውስጥ ዴሞክራሲ አካታችነትን በማጠናከር በዘመናዊ ፓርቲነት ሊኖራቸው የሚገባውን ተቋማዊ አቅም አጠንክሮ ለዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ስርአት ግንባታ ተጨባጭ ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻልም እንደሆነ ተነስቷል።
በአዋጁ እና በዚህ መመሪያ መሰረትም የፖለቲካ ፓርቲዎች ከመንግስት የሚያገኙትን ይህንን ድጋፍ ህጋዊ ስራዎችን እና ሃላፊነቶችን ለመወጣት ጥቅም ላይ ማዋል ያለባቸው ነው።
በተለይም የዜጎችን ፖለቲካዊ ግንዛቤ ለማሳደግ እንዲሁም የሴቶችን እና የአካል ጉዳተኞችን የፖለቲካ የተሳትፎ አቅም እና መጠንም ከፍ ለማድረግ ለማስቻል የሚውል ድጋፍ ነውም ነው የተባለው።
ይህ መመሪያ በቦርዱ ህጋዊ እውቅና በተሰጣቸው ሃገራዊ እና ክልላዊ ፓርቲዎች ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡
በመሆኑም ድጋፉ በእኩልነት እና ያለ አድልኦ የሚከፋፈል እንደሆነም በውይይቱ ተጠቁሟል።
በይስማው አደራው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.