Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ሁለተኛ ምእራፍ የከተማ ልማት ሴፍቲኔት መርሃ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኢንተርፕራይዝ እና
ኢንዱስትሪ ልማት ሁለተኛ ምእራፍ የከተማ ልማት ሴፍቲኔት መርሃ ግብር ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡
ሁለተኛ ምእራፍ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች 120 ወረዳዎች እና በ827 ክላስተር ማእከል ለመለየት ተችሏል።
የምግብ ዋስትና ፕሮግራም በከተማዋ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በ11 ከተሞች የተተገበረ ሲሆን፥ አመርቂ ውጤት በማሳየቱ በያዝነው በጀት አመት አዳዲስ 72 ከተሞችን በመጨመር እየተሰራ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፥ ድህነትን መቀነስ ብሎም ማስወገድ የሚቻለው የተገኘን ሀብት ወደ ስራ በመቀየርና ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ እንደሆነ ሊታመን ይገባል ነው ያሉት።
በአዲስ አበባም ለድህነት ቅንሳ ስራችን አጋዥ የሆኑ አጋሮቻችን በሚለግሠት ብድርና እርዳታ ላለፉት አመታት ስኬታማ ስራዎችን በማከናወን ለሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ምሳሌነቷን ከማሳየት ባሻገር በውጤቱም አያሌ ዜጐችን ተጠቃሚ ስታደርግ ቆይታለች ወደፊትም ታደርጋለች ብለዋል።
ሁለተኛው ምእራፍ በሀገራችን ደረጃ እውን እንዲሆን ከአለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት ከተገኘ 300 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ብድር እና የሀገራችን መንግስት 150 ሚሊየን ዶላር በድምሩ 450 ሚሊዮን ዶላር የተመደበ ሲሆን ለከተማዋ ነዋሪዎች የዚሁ በጀት 70 በመቶ በመመደብ ወደስራ ተገብቷል ብለዋል ።
በመጀመርያ ዙር 37 ወረዳዎች ከ102 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ለሶስት አመት ከአመለካከት እስከ ቴክኒክ ስልጠና በመስጠት በቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ፣ በውበት እና በአረንጓዴ ልማት ስራዎች ፣ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ፣ የከተማ ግብርና እና አነስተኛ መሰረተ ልማት ላይ በማሳተፍ አመርቂ ውጤት ተገኝቷል።
በቅድስት ተስፋዬ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.