የሀገር ውስጥ ዜና

የተማሪዎች መረጃን በማሸሽ ከህወሓት ወራሪ ቡድን ውድመት የታደጉት ግለሰብ

By Meseret Awoke

January 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ሐይቅ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ መሃመድ ኢብራሂም ለሁለት አስርተ ዓመታት የነበረውን የተማሪዎች የትምህርት ማስረጃ ከወራሪው ቡድን በማሸሽ ከውድመት ታድገውታል፡፡

ግለሰቡ ወራሪ ቡድኑ ከመግባቱ በፊት የሀይቅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ከ1995 እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ ያለውን ጠቅላላ የተማሪ መረጃ በአካባቢው በሚገኙ የግለሰብ ቤት በማስቀመጥ በትምህርት ቤቱ የሚማሩ እንዲሁም ከዚህ በፊት የተማሩ ተማሪዎችን መረጃ ከወድመት ታድገዋል፡፡

ግለሰቡ ከዚህም በተጨማሪ የቻሉትን ኮምፒዩተር በማሸሽም ከወራሪ ቡድኑ መታደግ ችለዋል፡፡

አቶ መሃመድ የፈፀሙት ተግባር እጅግ እንደሚያስመሰግን የተገለጸ ሲሆን ፥ ትምህርት ቤቱን መልሶ ለመገንባትን የመማር ማስተማር ስራውን ለማስጀመር ሁሉም ድጋፍ በማድረግ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

የህወሓት ወራሪ ሃይል በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በሙሉ የትምህርት ተቋማትን የጦር ካምፕ በማድረግ የቻለውን በመዝረፍ ያልቻለውን በማውደም መረጃዎችን በማቃጠል እንዲሁም የመቃብር ስፍራ በማድረግ ለህዝብ ያለውን ጥላቻ ማሳየቱን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!