Fana: At a Speed of Life!

ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኮሚሽነሮች ጥቆማ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኮሚሽነሮች ጥቆማ ተጀመረ፡፡

ጥቆማው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥር 6 ይቆያል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ መግለጫ የሰጡ ሲሆን ÷ አፈጉባኤው ኢትዮጵያን በጠንካራ መሰረት ላይ ለማስቀመጥ ቁልፍ ሚና ያለው አገራዊ ምክክር ውጤታማ እንዲሆን 11 ኮሚሽነሮች እንደሚሾሙ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያዊያን ለአገራዊ ምክክሩ ስኬት በንቃት መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል ያሉት አፈጉባኤው ÷ አጠቃላይ የኮሚሽነሮች ምርጫ ሂደት በአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን ይጠናቀቃል ብለዋል።

ለዚህም ውጤታማነት በአዋጁ ስልጣን ከተሰጣቸው የምክር ቤቱ አፈጉባኤ በተጨማሪ ከፌዴራል ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ፣ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሀፊና የሲቪክ ማህበራት የተካተቱበት አማካሪ ኮሚቴ መቋቋሙን ተናግረዋል።

በጥቆማው ላይ ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችሉ ግለሰቦች እንዲጠቆሙ የጠየቁ ሲሆን ÷ ከዛሬ ጀምሮ መጠቆም ይቻላል ብለዋል።

የጥቆማ ቅፆችም በምክር ቤቱ ድረገፅ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

አፈወርቅ እያዩ እና የሸዋ ማስረሻ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.