የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ለመላው አፍሪካ ሁለተኛ ሀገር ናት – የሴኔጋል አምባሳደር

By Meseret Awoke

January 04, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለመላው አፍሪካ ሁለተኛ ሀገር ናት ሲሉ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙት የሴኔጋል አምባሳደር መሀመድ ላሚን ቲያው ገለጹ፡፡

አምባሳደሩ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኘሮቶኮል ጉዳዮች ምክትል ሹም ለሆኑት አምባሳደር ዓለማየሁ ሰውአገኝ አቅርበዋል።

በወቅቱም ተሿሚ አምባሳደሩ ኢትዮጵያ ለመላው አፍሪካ ሁለተኛ ሀገር መሆኗን ጠቅሰው ÷ ሴኔጋል ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፍላጎት መኖሩን ተናግረዋል።

በሥራ ቆይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል በባሕል እና ቱሪዝም ዘርፎች ያለውን ትብብር ለማስፋት እና በኢንዱስትሪ ፓርክ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ልምድ ለመቅሰም እንደሚፈልጉም ጠቁመዋል።

አምባሳደር ዓለማየሁ በበኩላቸው ÷ ሴኔጋልና ኢትዮጵያ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አንስተው ÷ የሁለቱ ሀገራት ህዝቦችም ይበልጥ ተጠቃሚ በሚያደርጉ መስኮች ላይ አተኩረው መሥራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

አምባሳደሩ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው የሥራ ቆይታ የተሳካ ስራ ማከናወን እንዲችሉ ተገቢው ትብብር እንደሚደርግላቸውም አምባሳደር ዓለማየሁ እንዳረጋገጡላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!