Fana: At a Speed of Life!

የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ተጣለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ጥሏል፡፡

ቢሮው በመዲናዋ በሞተር ብስክሌት ምክንያት የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችንና ህገ ወጥ ድርጊቶችን መከላከል የሚያስችል የሞተር ብስክሌት ፈቃድና ቁጥጥር መመሪያ በማውጣት ወደስራ መገባቱ ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት ውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ በርካታ የዲያስፖራ አባላት ወደ ሀገራቸው እየገቡ ይገኛል፡፡

በተያያዘ ወቅቱ የበዓል ሰሞን እንደመሆኑ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ከቦታ ቦታ በብዛት እንቅስቃሴ እያደረጉ ሲሆን፥ ይህን ተከትሎ በከተማዋ የትራፊክ መጨናነቅ እና የዝርፊያ ምልክቶች እየታዩ ነው፡፡

ስለሆነ ከታህሳስ 22/2014 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ ቁጥጥር እንዲደረግ እና እርምጃ እንዲወሰድ ቢሮው ለሚመለከተው አካል የስራ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.