Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ በኔፓልና በባንግላዲሽ ከሚገኙ የክብር ቆንሥላዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 26፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በሕንድ የኢትዮጵ አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ መቀመጫቸውን በኔፓልና በባንግላዲሽ ካደረጉ የኢትዮጵያ የክብር ቆንስላዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታን የተመለከተ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።
አምባሳደሯ በውይይታቸው የህወሓት የሽብር ቡድን በአማራ እና በአፋር ክልሎች ያደረሰውን አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የመሰረተ ልማት ውድመት በተመለከተ እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋምና እያደረገ ያለውን ጥረት በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁሉን ያሳተፈ ውይይት ለማድረግ የብሔራዊ የውይይት ኮሚሽን ስለመቋቋሙም አምባሳደሯ ገልጸዋል።
አምባሳደሯ አክለውም ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች እና የኢትዮጵያ ወዳጆች “በቃ” በሚለው ዘመቻ ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን እንዲሁም በሽብር ቡድኑ የወደሙ መሠረተ ልማቶችን ለመገንባት ዳያስፖራዎች የገንዘብ እርዳታ እያደረጉ መሆኑን አብራርተዋል።
አምባሳደሯ በኢትዮጵያ በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን ጎብኝተው በመልሶ ግንባታ መርሃ ግብሩ ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉም ለቆንስሎቹ ጥሪ አቅርበዋል።
የክብር ቆንስላዎቹ በበኩላቸው አምባሳደሯ ላደረጉት ቅን ውይይት አመስግነው በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ግንዛቤ በመፍጠር የመንግስትን መልሶ የማቋቋምና የመልሶ ግንባታ ስራዎችን ለመደገፍ የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.