Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ በአንድ ቀን ብቻ ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ በአንድ ቀን ብቻ ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተነገረ።
ዩናይትድ ስቴትስ በአንድ ቀን ብቻ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባት ግንባር ቀደም ሀገርም ሆናለች።
ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ እንዲሆን ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ የኦሚክሮን ዝርያ በከፍተኛ ፍጥነት መዛመቱ ነው፡፡
በሀገሪቱ በዛሬው ቀን ብቻ 1 ሚሊየን 80 ሺህ የኮቪድ-19 አዲስ ታማሚዎች ተመዝግበዋል።
በሀገሩቱ የበሽታው ስርጭት ቁጥር ካለፈው ሳምንት በእጥፍ መጨመሩን መረጃው ያሳያል፡፡
አሜሪካ ይህንን ከፍተኛ የኮቪድ ታማሚዎች ቁጥር ያስመዘገበችው የሀገሪቱ ከፍተኛ የወረርሽኝ ጉዳዮች አማካሪ አንቶኒ ፋውቺ ወረርሽኙ በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ እንደሆነ ካስጠነቀቁ ከአንድ ቀን በኋላ ነው፡፡
እስካሁን በአለም አቀፍ ደረጃ 292 ሚሊየን ሰዎች በኮቪድ-19 የተያዙ ሲሆን፥ 5 ነጥብ 4 ሚሊየን ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን ማጣታቸውን ቲአርቲ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 14 people, people standing and outdoors
0
People reached
0
Engagements
Distribution score
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.