Fana: At a Speed of Life!

ዲያስፓራዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአፋር ካሳጊታ ግንባር ተገኝተው ጦሩን የመሩበትን ቦታ  ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዲያስፓራዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአፋር ካሳጊታ ግንባር ተገኝተው ጦሩን የመሩበትን ቦታ ጎብኝተዋል።

የካሳጊታ ተራሮችን በመያዝ ሚሌን አሻግሮ በመመልከት ይዘናል የሚል ተስፋ ሰንቆ ቢቆይም በግንባሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተገኝተው በሰጡት አመራር  ፥  በአፋር ልዩ ሀይል እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት በከፈሉት ዋጋ ህልም ሆኖበት ቀርቷል።

በዚሁ ግንባር ጠቅላይ ሚኒስተሩ  ከአፋር ክልል ርእሰ መስተዳደር አወል አርባ ጋር በመሆን በሰጡት አመራር ከፍተኛ ስልታዊ ድል የተገኘበት መሆኑ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዘመቱ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ አመራር እየሰጡ የታዩበትም ቦታ ነው።

መሪዎቹ በቦታው ተገኝተው አመራር የሰጡበትን ቦታ ነው ዲያስፓራዎቹ  የጎበኙት።

ካሳጊታ ጁንታው ከባቲ ከባድ መሳሪያዎችን በመላክ ለድል ለመብቃት ወሳኝ አድረጎ የተመለከተው እና ደረስኩ እያለ የቃዠበት ስፍራ ነው።

ታሪካዊውን ድል ለመቀዳጀት ታሪክ የተሰራበትን ቦታ በማየታቸው ዲያስፓራዎቹ መደሰታቸውን ተናግረዋል።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.