Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ፡፡

በጣሊያን ፔሩጂያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች በአሻባሪው የወያኔ ቡድን ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች በሁለተኛ ዙር ያሰባሰቡትን ከ6 ሺህ ዩሮ በላይ ገቢ አድርገዋል።

አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ ስለተደረገው ድጋፍና ድጋፉን ላደረጉት ወገኖች ምስጋና አቅርበዋል።

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑም ፥ አገራችን የገጠሟትን ተግዳሮቶች እስክትሻገር ድረስ ድጋፋቸውን አጠናከረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።

በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለተጎዱ ወገኖች እና ለወደሙ መሰረተ ልማቶች መልሶ መገንቢያ የሚውል 20 ሺህ 800 ድርሃም በተወካዮቻቸው አማካይነት ለዚሁ ዓላማ በተከፈተው የባንክ አካውንት ገቢ አድርገዋል፡፡

በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ “ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም” በሚል ስያሜ በማህበር የተደራጁት እነዚህ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄነራል ጽህፈት ቤት በመገኘት ነው ድጋፉን ያደረጉት፡፡

አባላቱ ለሀገራዊ ጥሪ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን በተግባር በማሳየታቸው ጽህፈት ቤቱ ምስጋናውን ማቅረቡን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.