Fana: At a Speed of Life!

ወደ አገር ቤት እየገቡ ያሉ ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው ቀጥለዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም ከውጭ ወደአገር ቤት እየገቡ ያሉ ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው መቀጠላቸው ተገልጿል፡፡

ዛሬም ከዲሲ ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በበረራ ወቅት በአውሮፕላን ውስጥ ያሰባሰቡትን 11 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተዘጋጀው የአይዞን ኢትዮጵያ አካውንት ገቢ አድርገዋል።

ዳያስፖራዎች በግልና በቡድን ከሚያደርጉት ድጋፍ በተጨማሪ ነው በጉዞ ላይ ገንዘብ በማሰባሰብ በጦርነቱ የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ድጋፍ እያደረጉ የሚገኙት።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዛሬ ማለዳ በርካታ ተጽዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በታላቁ ጉዞ ወደ አገር ቤት አዲስ አበባ መግባታቸውን ለመታዘብ ችሏል፡፡

በቆንጅት ዘውዴ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.