የሀገር ውስጥ ዜና

ወደ አገር ቤት እየገቡ ያሉ ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው ቀጥለዋል

By Feven Bishaw

January 05, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም ከውጭ ወደአገር ቤት እየገቡ ያሉ ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው መቀጠላቸው ተገልጿል፡፡

ዛሬም ከዲሲ ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በበረራ ወቅት በአውሮፕላን ውስጥ ያሰባሰቡትን 11 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተዘጋጀው የአይዞን ኢትዮጵያ አካውንት ገቢ አድርገዋል።