Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ሸዋ ዞን በሽብር ቡድኑ ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ ትምህርት ቤቶች ትምህርት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አሸባሪው ህወሓት ጉዳት ያደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች ወደ መማር ማስተማር ስራቸው እንዲገቡ እያደረገ መሆኑን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ገለጸ።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ በድሉ ውብሸት ÷ ወራሪ ቡድኑ በዞኑ በትምህርት ተቋማት ላይ ከ50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ትምህርት ቤቶቹ የመማር ማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።

በዞኑ በወራሪ ቡድኑ የከፋ ጉዳት ከደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል በጣርማበር ወረዳ ከሚገኘው መሶቢት ትምህር ቤት ውጪ በሌሎቹ ትምህርት መጀመሩን ነው ሃላፊው የገለጹት።

መሶቢት ትምህርት ቤት የከፋ ጉዳት ደርሶበታል ያሉትአቶ በድሉ ፥ ችግሩን በፍጥነት ለመፍታት እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ ህወሓት በሰሜን ሸዋ ዞን 180 ትምህርት ቤቶች ላይ ዘረፋና ውድመት መፈጸሙን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በግርማ ነሲቡ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.