Fana: At a Speed of Life!

የታሪክ አለመግባባቶችን ለመፍታት የዘርፉ ምሁራን የበኩላቸው ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የታሪክ አለመግባባቶችን ለመፍታት የዘርፉ ምሁራን የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን ያዘጋጀው “የታሪካዊነት አበርክቶ ለብሔራዊ መግባባትና የታሪክ ምሁራን ሚና” በሚል ርዕስ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ÷ በታሪኮች ላይ መግባባት ላይ የማንደርሰው ታሪኮችን የምንተርክበትና የምንተረጉምበት መንገድ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በዚህም ከትናንት ታሪኮቻችን ተምረን ለሰላምና እድገታችን ለመጠቀም ይቻል ዘንድ ምሁራን የበኩላቸውን ሚና መወጣት ይኖባቸዋል ነው ያሉት።

በውይይት መድረኩ የዘርፉ ምሁር ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ÷ “የታሪክ ግንዛቤዎችና የተሳሳተ አመለካከት” በሚል የመነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል።

ፕሮፌሰር ባህሩ ሙያዊ የታሪክ አጻጻፍ አለመኖር ለታሪክ መዛነፍ ምክንያት ከሆኑት ችግሮች ውስጥ አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የታሪክ ምንጭ አለመጥራትም ሌላኛው ችግር መሆኑን በጽሑፋቸው አብራርተዋል ።

ፕሮፌሰሩ በመነሻ ጽሁፋቸው የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት፣ ሁሉም ልክ፤ ሁሉም ስህተት ነው የሚል እይታ ለታሪክ አለመግባባት መነሻ እንደሚሆንም አስረድተዋል

አሁን ላይም ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው “በብሔራዊ መግባባት እና የሰላም ግንባታ የምሁራን ሚና” በሚል መነሻ ጽሁፋቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ።

በመድረኩ ምሁራን፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡

በምስክር ስናፍቅ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.