Fana: At a Speed of Life!

ሀገራችን በምትፈልገን ዘርፍ ሁሉ ለማገልገል ዝግጁ ነን- ዳያስፖራዎች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራችን በምትፈልገን ዘረፍ ሁሉ ለማገልገል ዝግጁ ነን ሲሉ የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገራቸው የመጡ ዳያስፖራዎች ገለጹ፡፡

አቶ ታሪኩ ተገኘ እና አቶ ገብረ አማኑኤል ተገኔ የኢትዮጵያን ጥሪ ተቀብለው ከኦስትሪያ ቬና እና ከአሜሪካ ወደ ሀገራቸው የገቡ ዳያስፖራዎች ናቸው፡፡

ዳያስፖራዎቹ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ የውጪው ዓለም ኢትዮጵያን የጦር ቀጠና አድርጎ ቢስላትም መጥተን የተመለከትነው ግን ከሚባለው ተቃራኒ ነው ብለዋል።

በኦስትሪያ ለ35 ዓመት የኖሩት አቶ ታሪኩ ተገኘ ወደ ሀገራቸው በመመለሳቸው መደሰታቸውን ገልጸው÷ በወደሙ አከባቢዎች የሚደረገውን መልሶ ግንባታ ለመደገፍ እየሰራን ነው ብለዋል።

በአሜሪካ ለ18 አመት የቆዩት አቶ ገብረአማኑኤል ተገኔ በበኩላቸው÷ በውጭ ያሳካነውን የበቃ እንቅስቃሴ በልማቱ ዘርፍ በመድገም ለእናት ሀገራችን በምንፈለገው ዘርፍ እንሰራለን ነው ያሉት፡፡

የዳያሰፖራ ማህበረሰብ አባላቱ በአፋር ክልል ባደረጉት ጉብኝት የሽብር ቡድኑ ህወሓት የፈጸመውን አሰቃቂ ድርጊት መመልከታቸውን አብራርተዋል፡፡

በቀጣይም በደቡብ ወሎና ደሴ ከተማ በሽብር ቡድኑ የተፈጸሙ ጉዳቶችን እንደሚጎበኙ ነው የገለጹት።

አሸባሪው ቡድን የዜጎችን አንገት ለማስደፍት ጥረት ቢያደርግም ዳያስፖራዎች የወደሙትን ከመገንባት ባለፈ በኢንቨስትመንት ተሳትፈን ሀገራችንን ከፍ ማድረግ አለብን ሲሉም አሳስበዋል፡፡

በከድር መሀመድ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.