Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ የባላስቲክ ሚሳኤል ወደ ባህር አስወነጨፈች

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 27፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ የባላስቲክ ሚሳኤል በተሳካ ሁኔታ ወደ ባህር ማስወንጨፏን አስታወቀች፡፡
 
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ባለፈው ሳምንት በገዢው ፓርቲ ኮንፈረንስ ላይ የሀገሪቱን ወታደራዊ አቅም የበለጠ ለማሳደግ ቃል መግባታቸው ይታወሳል፡፡
 
ይህን ተከትሎም ፒዮንግያንግ በተያዘው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገሪቱ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ በተሳካ ሁኔታ የባላስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፏ ተነግሯል፡፡
 
የደቡብ ኮሪያ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ጉዳዩን አስመልክቶ አስቸኳይ ስብሰባ ያደረገ ሲሆን÷ በዚህም የሰሜን ኮሪያው የባህር ዳርቻ ሚሳኤል ለደቡብ ኮሪያ የደህንነት ስጋት መሆኑን የገለጸው፡፡
 
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ በበኩላቸው÷ ሰሜን ኮሪያ የፈለገችውን የሚሳኤል አይነት ማስወንጨፍ እንደምትችል ገልጸው÷በጉዳዩ ዙሪያ ምንም አይነት የደህንነት ስጋት እንደሌለባቸው መናገራቸውን ሲጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.