Fana: At a Speed of Life!

የዳያስፖራውን አቅም ለመጠቀም ፍላጎቱን ማወቅና የኢንቨስትመንት አማራጮችን ማስፋት ያስፈልጋል- ሳይንቲስት ዶ/ር ጌታቸው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) የዳያስፖራውን አቅም ለመጠቀም ፍላጎቱን መለየትና የኢንቨስትመንት አማራጮችን ማስፋት ያስፈልጋል ሲሉ የባዮ ሜዲካል ሳይንቲስቱ ዶክተር ጌታቸው አበበ ገለጹ፡፡
 
ዶክተር ጌታቸው ከፋና ቴሌቪዥን ጋር ̎እኔም ለሃገሬ̎ በሚል መሪ ሃሳብ ባደረጉት ቆይታ÷ ከ18 ዓመታት የውጪ ሀገር ቆይታ በኋላ መንግስት ያቀረበውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር መግባታቸውን አንስተዋል፡፡
 
ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጅ ዳያስፖራዎች በ˝በቃ ˝ ንቅናቄ የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም ሲሳተፉ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡
 
የውጭ ጫናው በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲና በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደርገ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ጌታቸው ÷ ጫናውን ለመቋቋምም ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት፣ ገንዘብን በህጋዊ መንገድ መላክ እና ሌሎች የገበያ አማራጮችን ማፈላለግ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
 
በአደዋ ዘመቻ በርካታ አገራት ነጻ ለመውጣት ይታገሉ እንደነበር ጠቅሰው÷ አሁንም መሰል ፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ እየታየ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
 
ከዚህ በፊት ምዕራባውያ በሌሎች አገራት ላይ ያደርጉት የነበረውን ጫና እና ደባ ብዙ ሰው ግንዛቤ ስላለው እንዲነቃ አድርጎታልም ነው ያሉት፡፡
 
አንዳንድ ምዕራባውያን ዜጎች መንግስታቸው በሌሎች አገራት ላይ የሚያደርገውን ጫና ሲረዱ ይገረማሉ የሚሉት ዶክተር ጌታቸው ÷ ኢትዮጵያ ላይ የነበረውን እውነታ ለማስረዳት ሲጥሩ መቆየታቸውንም አስታውሰዋል፡፡
 
ኢትዮጵያውያን የራሳችንን እድል በራሳችን መወሰን አለብን ብለው ሲነሱ የውጭ ሃይሎች ኢትዮጵያን የሚያዩበት መነጽር እየተቀየረ መምጣቱንም አውስተዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እየተጠናቀቀ ሲመጣ የማይደሰቱ አካላት እንዳሉ ጠቅሰው÷ አንዳንድ አገራት ፍላጎታቸው ተፈጻሚ እንዲሆንና ጥቅማቸው እንዲጠበቅ የፖለቲከኞችን ሃሳብ በገንዘብ ለመቀየር ሲሞክሩ ይስተዋላል ብለዋል፡፡
 
የተለያዩ ፍላጎት ያላቸው ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነው የውጭ ጫናንና አሸባሪውን የመከቱት÷ ቡድኑ እድል ኖሮት ወደ ስልጣን ቢመጣ ምን ሊሰራ እንደሚችል ስለተገነዘቡ ነው ብለዋል፡፡
ከውጭ የሚገቡ አንዳንድ ምርቶችን ሀገር ውስጥ ማምረት እንደሚቻል እና በቀላሉ የሚቀየሩ ብዙ ነገሮች እንዳሉም ጠቁመዋል፡፡
 
በየሻምበል ምህርት
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.