የሀገር ውስጥ ዜና

በእስልምና ቅርስና ሃብት ላይ የደረሰውን ጉዳት እንደሚያጣራ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ

By Meseret Awoke

January 05, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በአማራ እና አፋር ክልሎች በፈፀመው ወረራ ወቅት በእስልምና ቅርስ እና ሃብት ላይ የደረሰውን ጉዳት እንደሚያጣራ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።

ጉዳቱን የሚያጣሩ ቡድኖች ከነገ ጀምሮ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች እንደሚያቀኑ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በሰሜን ወሎ ብቻ ከ30 በላይ መስጊዶች መቃጠላቸውን ከአሁን ቀደም በተደረጉ የዳሰሳ ጥናቶች ማወቅ መቻሉን ኢቢሲ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!