Fana: At a Speed of Life!

በአብዬ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ከአካባቢው ማህበረሰብ ሽልማት ተበረከተለት

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአብዬ ግዛት የሚገኘው የ25ኛ ሞተራይዝድ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አስተማማኝ ሰላምን በማስፈን ላበረከተው ታላቅ አስተዋጽኦ ከአካባቢው ማህበረሰብ የእውቅናና የምስጋና ሽልማት ተበረከተለት፡፡

የሻለቃው የግዳጅ ቀጣና በሆነውና ዱንግ አፕ በተባለ ስፍራ የሚኖሩት የንጎክ ዲንካ ማህበረሰብ የ2022 የአዲስ አመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ባዘጋጁት ልዩ ፕሮግራም ላይ ለ25ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ሌንጮ ኤደኦ ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡

የተበረከተላቸው ሽልማትም በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ክብርና ስፍራ የሚሰጣቸውና ትልልቅ የጎሳ መሪዎች የሚለብሱት ባህላዊ አልባሳት፣ የአንገት ጌጥ እና ባህላዊ ከዘራን ያካተተ ነው፡፡

ዋና አዛዡ ‘‘በአብዬና አካባቢው ቀንና ሌሊት እንዲሁም ክረምት ከበጋ ያለምንም መታከት ደከመን ሰለቸን ሳንል የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ፈተናዎችን በጽናት ተጋፍጠን በማለፍ ከህብረተሰቡና ከአጎራባች ክፍሎች ጋር ተቀራርበን በጋራ በመስራታችን የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ ችለናል’’ ብለዋል፡፡

ማህበረሰቡ ሰላማዊ ኑሮ መምራት በመቻሉ በየጊዜው በሚከበሩ ሃይማኖታዊና ሌሎች በዓላት ወቅት ለሰራዊቱ የተለያዩ ስጦታዎችን ሲያበረክት መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

የአሁኑ ሽልማትም እንደ አገርም ሆነ እንደ ሻለቃ ትልቅ ስኬትና ኩራት በመሆኑ በቀጣይ ለሚፈፅሟቸው ግዳጆች ትልቅ የሞራል ስንቅና መነቃቃትን የሚፈጥርላቸው መሆኑን መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.